=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
የሰው ልጅ ሆይ ከረሃብ በኃላ ጥጋብ አለ ፣ ከጥማት በኃላም እርካታ አለ ፣ ከእንቅልፍ እጦት በኃላም እንቅልፍና ከበሽታ በኃላ ጤና አለ። የጠፋው ይገኛል ፤ የጠመመውም ይቃናል ፤ በአይን የተበላውም ይድናል ፤ ጨለማውም ይገፋል።
-<({አልቁርአን 76:9})>-
«አሏህም ድልን ወይም ከርሱ ዘንድ የኾነን ነገር እንዲያመጣ ይከጅላል።»
በተራሮች ላይ እና በየሸለቆዎቹ የሚያሳድደው ንጋት እንደሚመጣ ሌሊትን አብስረው ፣ የተጨነቀውንም ሰው በዓይን ጨረፍታ እና በብርሃን ፍጥነት የሚደርስ ድንገተኛ መፍትሄ እንደሚገኝ አብስረው ፤ አደጋ የደረሰበትንም ሰው ድብቅ መዳኛ እነደሚያገኝም አብስረው። በረሃው እየሰፋ መሆኑን ካየህ አረንጏዴ መስኮች እንደሚከተሉ እወቅ። ገመድም በኃይል ከተጎተተ እንደሚበጠስ እወቅ።
እምባን ተከትሎ ፈገግታ አለ ፤ ፍርሃትን ተከትሎ አማን ፣ ድንጋጤን ተከትሎ መረጋጋት አለ። ወደ አሏህ አንድነት የሚጣራውን ኢብራሂም እሳት ልታቃጥለው አልቻለችም ምክኒያቱም መለኮታዊው እንክብካቤ እሳትን «ቀዝቃዛና ሰላም ሁኚለት» የሚለውን የእዝነት መስኮት ከፍታለታለችና።
ባህሩም ሙሳን አላሰመጠችውም ምክኒያቱም እውነተኛውና ኃያሉ ድምፅ «ጌታዮ አብሮኝ አለ ይረዳኛልም» ብሏልና።
ነብዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ ዋሻ ውስጥ ጏደኛቸውን ሲያፅናኑ «አሏህ ከኛጋር ነው» አሉ። በዚያም አማንን እርጋታንና በመጨረሻም ድልን አገኙ።
የአስቸጋሪ ጊዜያቸውና የነባራዊ ሁኔታቸው ባሮች ሁሌም የሚታያቸው ጥበት ፣ ችግር እና እድለቢስነታቸው ብቻ ነው። ምክኒያቱም ከቤቱ መግቢያ በር እና መስኮት ውጭ አሻግረው አይመለከቱም። ዓይኖቻቸውን ከግርዶው ጀርባ አሳልፈው ይመለከቱ ፤ አስተሳሰባቸውንም ከአጥሩ ጀርባ ያሻግሩ።
ራስህን አታጨናንቅ። ያለህበት መከራ እስከ መጨረሻው አይቀጥልምና ከዒባዳዎች(ከአምልኮዎች) በላጩ የአሏህን መፍትሄ መጠበቅ ነው። ቀናት ይገለባበጣሉ ፤ ዓመታትም ይለዋወጣሉ። የሩቅ ሚስጥሩም ድብቅ ነው። ጥበበኛውም ጌታ በየቀኑ በተለያዩ ጉዳዮች ውስጥ ነው ፤ ምናልባትም ከዚያ ብኃላ ሌላን ነገር ሊያስከትል ይችላል ፤ መከራንም ተከትሎ ምቾት ይመጣል።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|